አ
ዜና
← ዜናዎች
ዜና
news
የአብክመ ፕላንና ልማት ቢሮ በተለያዩ የስራ መደቦች ላይ ተቀጥረው የሚሰሩ ባለሙያወችን አወዳድሮ መቅጠር የሚያስችለውን ፈተና ሰጠ
የአብክመ ፕላንና ልማት ቢሮ በተለያዩ የስራ መደቦች ላይ ተቀጥረው የሚሰሩ ባለሙያወችን አወዳድሮ መቅጠር የሚያስችለውን ፈተና ሰጠ።
+++++
ግንቦት 27/2018 ባህር ዳር ( ፕላንና ልማት ቢሮ)፣ የአብክመ ፕላንና ልማት ቢሮ በተለያዩ የስራ መደቦች ላይ ተቀጥረው የሚሰሩ ባለሙያወችን አወዳድሮ ለመቅጠር የሚያስችለውን ፈተና ዛሬ ሰጥቷል።
ፈተናው በክልል ደረጃ ተዘጋጅቶ በአራት ማእከላት ማለትም በባህር ዳር፥ በደብረ ብርሀን፥ በደሴ እና በጎንደር ማአከሎች የተሰጠ ሲሆን ተፈታኞችም ክልሉ እና ዞኖች ባወጡት የስራ ቅጥር ማስታወቂያ መሰረት መስፈርቱን አሟልተው የተመዘገቡ ተወዳዳሪወች ናቸው።
የተዘጋጀው ፈተና ለክልሉ ፕላንና ልማት ቢሮ በተፈቀዱ የማክሮ ኢኮኖሚ ጥናት ትንተና ባለሙያ IV፥ የማክሮ ፕላን ዝግጅት ባለሙያ IV፥ የኢንዱስትሪ ዘርፎች ኢኮኖሚ አካውንት ባለሙያ IV፥ የግብርናና ተዛማጅ ዘርፎች ኢኮኖሚ አካውንት ባለሙያ IV (በአጠቃላይ 6 ባለሙያወችን የሚይዙ የስራ መደቦች) ላይ እና ለሁሉም ዞንና ሪጆፖሊታን ከተሞች ፕላንና ልማት መምሪያወች የዘርፎች ፕላንና ፕሮጀክት ፕላን ዝግጅት ባለሙያ III (44 ባለሙያወችን የሚይዙ የስራ መደቦች) ላይ ተመድበው የሚሰሩ ባለሙያወችን አወዳድሮ ለመቅጠር ሲሆን መስፈርቱን አሟልተው ለፈተና የቀረቡት ተወዳዳሪወች ጠቅላላ ብዛት 254 መሆኑን እና ከዚህ ውስጥ 27ቱ ሴቶች መሆናቸውን የየማእከሉ አስተባባሪወች ገልጸዋል።
በዚህ ፈተና አልፈው በስራ መደቦቹ የሚመደቡ ባለሙያወች ጠቅላላ ብዛት 50 ሲሆን በቀጣይ በ25 አመቱ አሻጋሪ እድገትና ዘላቂ ልማት ፍኖተ-ካርታ እና በ5 አመቱ አሻጋሪ እድገትና ዘላቂ ልማት እቅድ ዙሪያ የግንዛቤ ማስጨበጫ ስልጠና እንደሚወስዱ ቢሮው ገልጿል።
በሁሉም ማእከላት አስተባባሪወችን መድቦ ፈተናውን እንዲሰጥ ያደረገበት ምክንያት ለስራ መደቦቹ ብቁ የሆኑ ባለሙያወችን በጥንቃቄ መምረጥ እንዲቻል መሆኑን ቢሮው ገልጿል።
Researching, innovating, influencing"

ተዛማጅ ዜናዎች
የ
ዜና
ዜና
Election 2026
የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ለ7ኛው ጠቅላላ ምርጫ የተቋቋሙ ልዩ ምርጫ ጣቢያዎች ላይ መራጮች ስለሚመርጡበት አግባብ ከፖለቲካ ፓርቲዎች ጋር ግንቦት 11 ቀን 2018 ዓ.ም. ተወያየ። የውይይቱን የመክፈቻ ንግግር የቦርዱ ሰብሳቢ ሜላትወር...
ተጨማሪ ያንብቡ →